የባንኩን 25 ዓመታት የምስረታ በዓልን ተከትሎ ሊከበሩ በዕቅድ ከተያዙ መካከል አንዱ የሆነው የንብ ባንክ ደንበኞች ቀን ታኅሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአዚማን ሆቴል ተከብሯል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በዚሁ ስነ ስርአት ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ የምንጊዜም የጀርባ አጥንት የሆኑትን ባለአክሲዮኖችና ደንበኞችን አመስግነዋል።
በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት (የሥራ) ዘርፍ ከተሰማሩት ከእነዚህ ደንበኞች ጋር በወደፊት በጋራ መሥራት አቅጣጫ ላይ ትኩረት አድርገዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር፣ ደንበኞች ባንኩ አጋጥሞት በነበረው የፈተና ጊዜ ፈተናውን እንዲወጣ ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበው፣ በቀጣይ አመታት ተስፋ የሰነቁ ስራዎች እንደሚሰሩ እምነታቸውን ገልጸዋል።
በበአሉ ላይ እውቅናና ምስጋና ተበርክቷል።
በመጨረሻም ያጋጠሙ ችግሮችን በጋራ በመፍታት የጋራ ውጤታማ ሥራዎችን ለማስመዝገብ በትጋት እንደሚሠሩ ቃል ገብተው የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።