Internet Banking
Internet Banking

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የባለአክስዮኖች 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የባለአክስዮኖች 26ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ አካሄዷል፡፡

ለጉባኤው አባላትና ተሳታፊዎች የእንኳ ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ሸዋነካ እ.ኤ.አ በ2024/25 በጀት ዓመት በተከናወኑ ስራዎች ላይ የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በበጀት አመቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ባንኩ ከፍተኛ ውጤቶች ማስመዝገቡን የገለጹ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በበርካታ መለኪያዎች ባንኩን እጅግ የተሻለ ደረጃ ላይ ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ይህም በተያዘው በጀት አመት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ የውስጥ አቅሙን በመጠቀም የ3 አመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እና የ5 አመት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት መተግበር እንደቻለ በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡  የባንኩን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች ለማዘመንና ለደንበኞቹ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማቅረብ እንዲረዳ ንብተራ የተሰኘ ዘመናዊ መተግበሪያ ሥራ ላይ መዋሉ ተገልጿል፡፡ ከተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት አንጻርም አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ተመልክቷል።

በመጨረሻም በቀረቡ ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ከባለአክሲዮኖች በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ውይይቶች ተደርጎ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡

***

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

<p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs