በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት አዳራሽ ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄደ፡፡
በምክክር መርሐ ግብሩ ላይ የባንኩ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በላይ ጎርፉ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በሩብ ዓመቱ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ መስተካከል በሚኖርባቸው ላይ በጋራ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የጋራ አቅጣጫ አስቀምጦ ለመውጣትም ሁሉም እንዲሳተፍ ጠይቀዋል፡፡
በመጨረሻም በቀጣይ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበት፣ ደካማ ጎኖችን በማረም ለውጤት መሥራት እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በስብሰባው የባንኩ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የመምሪያና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች እና የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ተገኝተዋል፡፡