ዛሬ ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በተከናወነው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የባንኩ ቺፍ እና ምክትል ቺፍ ኦፊሰሮችን ጨምሮ የዲስትሪክትና የመምሪያ ዳይሬክተሮች እንዲሁም የፕሪምየም ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ተሳትፈዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዚሁ መድረክ ባደረጉት ንግግር ሁሉም የባንኩ ከፍተኛ አመራር በኢንደስትሪው እና በባንኩ ውስጥ በሚመራው የሥራ ዘርፍ ይበልጥ ተወዳዳሪና ውጤታማ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የባንኩ አመራር የልዩ ብቃት ባለቤት እንዲሆን በመሰረታዊ የአመራር ክህሎትና ክፍተቶች ዙሪያ ያተኮረ አነቃቂ የስልጠና ምዕራፍ በማዘጋጀትም ገለጻ አድርገዋል፡፡
ጥራትና ፍጥነት መወዳደሪያ በሆነበት የባንኩ ኢንደስትሪ “ከፍተኛ አመራሩ ሊወዳደር ሳይሆን ልዩነት ሊፈጥር ይገባዋል”ም ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡
በዚህም በቀዳሚነት ለግል ሳይሆን ለተቋማዊ ፍላጎቶች ቅድሚያ በመስጠት፣ በራሱና በሚመራው ሰራተኛ መካከል ያለውን ግንኙነት ሚዛናዊነት በማረጋገጥ እንዲሁም ተግባራትን በዋነኛ የውጤት መለኪያ ላይ ተመስርቶ በማከናወን አመራሩ የተጣለበትን ሀላፊነት በትክክል ሊወጣ እንደሚገባም አቶ ሄኖክ አጸኖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
***
25 አመታትን በታታሪነትና በአገልጋይነት!
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!