የ2025/26 በጀት ዓመት የመጀመሪያው አጋማሽ የማኔጅመንት የምክክር መርሃ-ግብር አራት ኪሎ በሚገኘው የባንኩ የስብሰባ አዳራሽ ጥር 16 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሄደ፡፡
መርሃ-ግብሩን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ከከፈቱ በኋላ የመጀመሪያው ስድስት ወራት የሥራ-አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
ሪፖርቱን አስመልክቶም የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደተናገሩት፤ የባንኩ የስድስት ወራት ውጤት በሁሉም የአፈጻጻም መለኪያዎች ተገምግሞ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ ገልጸው፤ ከተቀመጠው ዕቅድ አንጻር ግን ከአሁኑ በላቀ ደረጃ መፈጸም አስፈላጊ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡
በቀሪዎቹ ስድስት ወራትም የተሻለ ውጤት በሁለም ዘርፍ ለማስመዝገብ ጠንካራ ሥራ መሰራት እንዳለበት ጠቁመው፤ መላው ሠራተኛ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ አጠናክሮ በመቀጠል እና ክፍተቶችን በማረም፣ በበጀት ዓመቱ ለመፈጸም የተያዙ ዕቅዶችን ለማሳካት ሁሉም አመራሮች እና ሠራተኞች ከምንግዜውም በላይ ተባብረው እና ጠንክረው እንዲሰሩ አደራ ብለዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች፣ የመምሪያና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፤ የበጀት ዓመቱ አጋማሽ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ጥልቅ ውይይት ከተደረገ በኋላ የምክክር መድረኩ ተጠናቋል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!









