ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 1447ኛውን የረመዷን የፆም ወር አስመልክቶ የገቢ ምንጫቸው አነስተኛ ለሆኑ ወገኖች ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጎሮ አንቢያ መስጊድ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አካባቢ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ድጋፍ ተደርጓል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአንቢያ መስጊድ አስተዳደር እና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተወካዮች ተገኝተው በዚህ ቅዱስ የረመዷን የፆም ወቅት እንዲህ ያሉ ድጋፎች መፈፀማቸው ወቅቱ የሚጠይቀው ሰደቃና መተሳሰብ መሆኑን ገልጸው ለባንኩ ምስጋና አቅርበዋል።
ተረጂዎቹም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ዱዓ እና ምስጋና በማቅረብ ይህ ዓይነቱ በጎ ተግባር በቀጣይም እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በባንኩ በኩል የተገኙት የምስራቅ እና የምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ኃላፊዎች እንዲሁም ዳይሬክተሮች ወቅቱ የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ እና ፈጣሪን የምናመሰግንበት መሆኑን ገልጸው፣ ባንኩ በቀጣይም በተለያዩ ከተሞችና ዲስትሪክቶች ተመሳሳይ የበጎ ድጋፍ ስራዎችን እንደሚቀጥ አመላክተዋል አስታውቀዋል።
ረመዷን ሙባረክ!!
አስር አመታት በሃላል አገልግሎት!
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!











