መንግሥት ለከተሞች ውበት በሰጠው ልዩ ትኩረት ባንካችንም ሃሳቡን በመደገፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎቹን ግዢ በማከናወን አስረክቧል፡፡
ስማርት የመብራት ፖሎቹን የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የፋሲሊቲስ ምክትል ቺፍ ኦፊሰር አቶ አሰፋ ጄዛ በኢንደስትሪ ሚኒስቴር ለቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት አስረክበዋል፡፡
ባንኩ ያበረከታቸው ዘመናዊ የመብራት ፖሎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የከተሞች ውበትና ልማት መርሐ-ግብር ለክልል ከተሞች በድጋፍ የሚሰጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡
25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው ባንካችን ባለ 37 ወለል ምስለ ንብ ቀፎ ህንጻ በማስገንባት ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን ልዩ ውበት ማላበሱ የሚታወቅ ነው፡፡
በማህበራዊ ሀላፊነት ረገድም ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከመንግሥት፣ ከግል ድርጅቶችና ከተለያዩ አካላት ለሚቀርቡለት የማህበራዊ ጉዳይ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጥ የቆየ የ”መልካም ስም” ባለቤት ነው፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!