N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የ2025/26 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የማኔጅመንት የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

ባንካችን የ2025/26 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የማኔጅመንት የምክክር መድረክ ዛሬ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት አካሄደ፡፡ ምክክሩ በተካሄደበት ወቅት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ ባንካችን በበጀት ዓመቱ ለመፈጸም ካስቀመጣቸው ተደራሽ ግቦች አኳያ የተጀመሩና አርዓያነት ያላቸው ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹ ሲሆን በሀብት አሰባሰብ፣ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት እንዲሁም ደንበኛ ተኮር የባንክ አገልግሎቶች ላይ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የሩብ ዓመቱ ጠንካራና ደካማ ጎኖች የተለዩና ሰፊ ውይይቶች የተካሄደባቸው ሲሆን፤ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል፣ ደካማ ጎኖችን ደግሞ በፍጥነት በማረም ባንኩን ወደ ላቀ የአፈጻጸም ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጦ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs