N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የ1447ኛውን የረመዷን ጾም ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር መርሃ-ግብር አካሄደ።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 1447ኛውን የረመዷን የጾም ወርን ምክንያት በማድረግ ከደንበኛቹ ጋር የኢፍጣር መርሃ-ግብር ትናንት የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል።

 

በኢፍጣር መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ሽዋነካ እንኳን ለታላቁ የረመዷን የጾም ወር በሠላም አደረሳቹሁ፤ ቀሪው የጾም ጊዜ በመከባበር፣ በመተሳሰብና በጸሎት የምናሳልፈው እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴ ነው ብለዋል፡፡

 

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸው ባንኩ የደንበኞቹን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት ጀምሮ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን ለደንበኞቹ እየሰጠ መሆኑን አስታውሰው አገልግሎቱ ወደፊትም በተጠናከረና ወቅቱ በሚፈልገው መልኩ ወደ ደንበኞቹ ይበልጥ በመቅረብ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ይሠራል ብለዋል።

 

የባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የተዘጋጀው የደንበኞቻችንን ልዩ ልዩ ፍላጎት ለማሟላትና የባንኩን አካታችነት በተግባር ለማሳየት እንደሆነ የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ ባንካችን በመቅረብ በስፋት እንዲጠቀሙበት እንጋብዛለን ብለዋል።

 

በሌላም በኩል የተጀመረው የረመዷን ጾም መልካም ሥራን በመስራትና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ ከፈጣሪ ጋር ግንኙነት የሚጠናከርበትና መንፈሳዊ ደስታ የሚገኝበት ወቅት መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህ የጸና መንፈስ ጾሙን እንድናጠናቅቅ ፈጣሪ ይርዳን ብለዋል።

 

በኤፍጣር መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም በበኩላቸወ ለመላው የሙስሊም ማኅበረሰብ እንኳን ለረመዷን ጾም አደረሳችሁ፣ አደረሰን የሙስሊሙ ማኅበረሰብም ጾምን ምክንያት በማድረግ መረዳዳት መተጋገዝ አለበት ያሉ ሲሆን ንብ ኢንተርናሽናል ባንክም ለሙስሊሙ ያለውን ክብር የኢፍጣር መርሃ ግብር በማዘጋጀት ላደረገው ዝግጅት በእጅጉ ሊመሰገን የገባል ብለዋል። በሌላም በኩል የባንኩ የሸሪአ አማካሪ ዶ/ር ሙሐመድዘይን ኑር ሁሴንም እንኳን አደረሳች የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

በመርሃ-ግብሩ ላይ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የማኔጀመንት አካላት፣ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ፣የባንኩ ደንበኞች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs