N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የንብተራ ኦንላይን ቲኬት መተግበሪያን በይፋ አስጀመረ።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የንብተራ ኦንላይን ሚኒ አፕ የሆነውን “ንብተራ ቲኬት” የተሰኘ አዲስ ዲጂታል አገልግሎት ዛሬ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ አስጀመረ።

የመተግበሪያውን በይፋ መጀመር ያበሰሩት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፤ ”ንብተራ ቲኬት” ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ የንብተራ ኦንላይን መተግበሪያ በመጠቀም የተለያዩ ሁነቶች ማለትም ቴያትሮች፣ ሲኒማዎች፣ ኮንሰርቶች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ሙዚየሞች እና ፓርኮች መግቢያ ትኬቶችን ንብተራ ኦንላይንን በመጠቀም በቀላሉ መቁረጥ ያስችላል።

መተግበሪያው ለሁነት አዘጋጆች እና አገልግሎት ሰጪዎች፤ ትኬቶቻቸውን ኦንላይን ያለምንም ሰልፍ እና እንግልት እንዲሸጡ፣ ሽያጫቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ሪፖርቶችንም በተደራጀ መልኩ እንዲያገኙ፣ የተለያዩ የክፍያ አማራጮችን እንዲጠቀሙ፣ ቅናሾችን እና የማስተዋወቂያ ሽያጮችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው።

አግልጋሎቱን ለማግኘት ደንበኞች የባንኩን ሒሳብ በመክፈት እና ንብተራ መተግበሪያን አውርደው መጠቀም እንደሚችሉ እና ትኬቱን ሲቆርጡ በስልካቸው የሚደርሳቸውን ”QR” ኮድ ለአዘጋጆች ማረጋገጫነት እንደሚያገለግል ተብራርቷል።

አገልግሎቱ ከወዲሁ በዘመን ሲኒማ የተጀመረ ሲሆን፤ ደንበኞች መጋቢት 27/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በሲኒማ ቤቱ የሚታዩ ፊልሞችን ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቲኬቱን በንበተራ ኦንላይን ለሚገዙ ደንበኞች የመግቢያ ቲኬቶችን በነጻ በመቁረጥ መታደም እንደሚችሉ ተገልጿል።

መተግበሪያው ለአጠቃቀም ምቹና ሙሉ በሙሉ በባንኩ የውስጥ አቅም በልጽጎ ለደንበኞች የቀረበ መሆኑ ተመልክቷል።

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs