ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከUN Women የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው ዕለት ፈርሟል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው የውይይት መርሐ ግብር ላይ ከተባበሩት መንግሥታት በኩል ሙካሩባጋ የድርጅቱ የኢትጵያ ተወካይ እንዲሁም በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በኩል ወ/ሮ ሐረገወይን አምሳለ የዓለም አቀፍ ባንክ አገልግሎት ም/ቺፍ ኦፊሰር የፊርማ ሥነ ሥርአቱን አካሄደዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሚመለከት ጠቃሚ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተለይ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ አቶ በግዱ ኃይለመስቀል የዳሰሳ ጥናት አቅርበዋል፡፡




