N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከጎዛም ቴክኖሎጂስ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረመ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከጎዛም ቴክኖሎጂስ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት ተፈራረመ።

በመግባቢያ ስምምነቱ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የባንኩ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ ከጎዛም ቴክኖሎጂስ ጋር የተደረገው ስምምነት ባንኩ ሥራ ላይ ያዋለውን አዲሱን የሦስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ እና የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ በቴክኖሎጂ በማገዝ ስኬታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦና እገዛ እንደሚኖረው አመልክተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የጎዛም ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጀነራል ማናጀር አቶ ናርዶስ መአዛ በበኩላቸው ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት በመስማማታቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ስምምነቱ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖጂ ውጤቶችን በመጠቀም በተለይም በዳታ አናሊቲክስ እና በዳታ ሞደርናይዜሽን እና ሌሎች ዘርፎች ዙሪያ ከባንኩ ጋር በመሥራት ለውጥ ለማምጣት እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡

የጎዛም ቴክኖሎጂስ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ በዳታ ሞደርናይዜሽን፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በሪስክ ማኔጅመንት፣ በአይቲ ኢንፍራስትራክቸርና አፕሊኬሽን እንዲሁም በፊንቴክ ኢኖቬሽን ዙሪያ የተለያዩ ሥራዎች የሚሠራ ዓለም አቀፍ ተቋም እንደሆነ በመርሐ ግብሩ ተመልከቷል፡፡

***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs