N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከያጉት ፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ዲጂታል ክፍያን የሚያዘምን “NIB ETHQR Sound Box Platform” በሥራ ላይ አዋለ።

ባንኩ ከያጉት ፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅት ጋር በመተባበር፤ የባንኩን ዲጂታል ክፍያ የሚያዘምንና ለደንበኞቹ ፈጣንና አስተማማኝ ክፍያ መፈጸም የሚያስችል “NIB ETHQR Sound Box Platform”፣ ዛሬ መስከረም 12 ቀን፣ 2019 ዓ.ም.፣ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በይፋ አስጀመረ።

“ሳውንድ ቦክሱ”፤ ነጋዴዎች ደንበኞቻቸው ላደረጉት ግብይት ክፍያ ሲፈጽሙ፤ ወዲያውኑ በድምጽ እንዲያውቁት በማድረግ የዕለት ተዕለት ግብይታቸው አስተማማኝ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ደህንነቱ በተጠበቀ መልክ መፈጸሙን ያረጋግጥላቸዋል፡፡

 

በማብሰሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ አቶ ሄኖክ ከበደ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የባንኩ አምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫ፤ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶቹን በማስፋፋት ለደንበኞች ቀላል፣ ፈጣን፣ አስተማማኝና ዘመናዊ የክፍያ መተግበሪያዎችን ለማቅረብ በከፍተኛ ትኩረት መስራት ላይ እንደሆነ ገልጸው፤ በሥራ ላይ እንዲውል የተደረገው “NIB ETHQR Sound Box Platform”፤ የዚሁ የትኩረት አቅጣጫ ማሳያ እንደሆነ አስረድተዋል። በቀጣይም ባንኩ የደንበኞቹን ተሞክሮ የሚያሻሽሉና የዲጂታል ኢኮኖሚውን የሚያጠናክሩ አዳዲስ የዲጂታል ባንኪንግና የክፍያ መፍትሄዎችን ለደንበኞቹ ለማቅረብ ተግቶ እንደሚሠራ ጠቁመዋል።

 

የያጉት ፔይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተሾመ ዓለማየሁ በበኩላቸው፤ ድርጅታቸው ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በመተባበር መስራቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው፤ ወደፊትም ለንግድ ተቋማት እና ለደንበኞች ቀላል፣ አስተማማኝና ዘመናዊ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን በማቅረብ፤ ሀገራችን የዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

 

በሌላም በኩል ባንኩና ያጉት ፔይ፣ የኦንላይን ክፍያ ትስስር መፍጠር (Payment Gateway)፣ የስማርት ፖስና የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አገለግሎት፣ የነዳጅ ተሽከርካሪዎች (Fuel Fleet) ማኔጅመንት፣ የንብተራ አስኳላ እና የንብተራ ቢዩልዲንግ የክፍያ አማራጮችን የማዘመን ሥራዎች በጋራ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

 

በመርሃ-ግብሩ ላይ የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ እና ማኔጅመንት አባላት፣ የያጉት ፔይ የቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የመገናኛ ብዙኃን አባላት ተገኝተዋል።

 

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs