ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከተክለሀይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በባንኩ ዋና መ/ቤት ለሚገኙ ሠራተኞች ነጻ የጤና ምርመራ እና የምክር አገልግሎት መርሃ ግብር ዛሬ ነሀሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት አካሄደዋል።
በመርሃ ግብሩ የተክለሃይማኖት ጠቅላላ ሆስፒታል 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ከሆስፒታሉ በመጡ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች አማካኝነት ለባንኩ ሠራተኞች ነፃ የጤና ምርመራ፣ የጤና ምክር እና የግንዛቤ ማስጨበጫ አገልግሎት ሰጥቷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባንኩ የማኔጅመንት አባላትም ሆስፒታሉ ላሳየው ዘላቂነት ያለው አጋርነትና በተለይም ለባንኩ ሠራተኞች ጤና በመጨነቅ ለሠጠው አገልግሎት አመስግነዋል።
በቀጣይም ሁለቱም ተቋማት የጀመሯቸውን ተቋማዊ አጋርነት የበለጠ በማጠናከር እንሚሠሩ ገልጸዋል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!



