ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከባንኩ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ጋር የአብሮነት የምክክር ጊዜ መርሃ ግብር ዛሬ ነሀሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ አካሄደ፡፡
መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ሸዋነካ ባንኩ ከባለአክሲዮኑ፣ ከደንበኛቹና ሠራተኞቹ ጋር በተሠሩ ቁርጠኛ የሆኑ ሥራዎች በሁሉም መለኪያዎች አበረታች ውጤትና ትርፍ በማስመዝገብ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ባለአክሲዮኖች የባንኩ መሠረቶችና አምባሳደር በመሆናቸው ከዚህ ቀደም ከነበረው ግንኙነት በተሻለ ከባንካችሁ ጋር በመሥራት የላቀ ውጤት ልናስመዘግብ ይገባል ብለዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸው ባንኩ አዲስ የ3 አመት ስትራቴጂ ቀርጾ እየሠራ መሆኑን በመጠቆም በተለይ የንብተራ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ደንበኛ ተኮርና ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች የሚሰጥ በመሆኑ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በተጠናከረ መልኩ እየተሠራ እንደሚገኝ አመልክተው ሁሉም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አንዲሆን መልእክት አስተላልፈዋል።
በአብሮነት የምክክር መድረኩ ላይ የተሳተፉ ባለአክሲዮኖችም ባንኩ እያደረገ ባለው ውጤታማ ሥራዎች መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣም ከባንካቸው ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር እንደሚሠሩ ጠቁመዋል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!



