N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በእንጦጦ ተራራ ላይ አካሄዱ፡፡

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እና እህት ኩባንያው ንብ ኢንሹራንስ ሠራተኞቾ  የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነውን ዓመታዊ የአገር በቀል ችግኞች ተከላ መርሃ ግብራቸውን ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር በተረከቡትና እንጦጦ በሚገኘው ተራራ ላይ ዛሬ ሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም አካሄደዋል።

 

 

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የንብ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ካለው ቁርጠኝነት በመነሳት በየአመቱ በርካታ አገር በቀል ችግኞችን የመትከል፣ የመንከባከብ እና ድጋፍ የማድረግ ሥራ ይሠራል ብለዋል፡፡

 

 

ባንኩ ችግኝ በመትከል ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን ባንካችን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ቋሚ አባል በመሆን ዘላቂ ድጋፍ በማድረግና በመንከባከብ ተገቢውን ሥራ እየሠራ ሲሆን ባለፈው አመት የተተከሉት ዛፎችም ሙሉ በሙሉ መጽደቃቸው ተገልጿል።

 

 

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሄኖክ አክለውም፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተሳሰረ መሆኑን አስታውሰው፣ ባንኩ ከንብ ኢንሹራንስ ጋር በጋራ የሚሠራቸው በጎ ተግባራትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

 

 

የንብ ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዙፋን አበበ በበኩላቸው በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸው የአካባቢ ጥበቃ ተግባሩን በቀጣይም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

 

 

በመጨረሻም፣ ለመርሃ ግብሩ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር እንዲሁም ሌሎች ምስጋና ቀርቦ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs