የተለያዩ ማኅበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣ የሚገኘው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከUSAID Healthy Behavior Activity ጋር በመተባበር የነፍሰ ጡር እናቶች ጤና ለማሻሻል የሚያግዝ “አራሼ” የተሰኘ አዲስ የቁጠባ ሒሳብ ትናንት በወልቂጤ ከተማ ይፋ አድርጓል፡፡
ንብ “አራሼ” የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ነፍሰ ጡር እናቶች በቅድመ ወሊድ ወቅት የጤና ክትትል ለማድረግ እንዲሁም ድህረ ወሊድ በተገቢው መንገድ መታረስ እንዲችሉ ከሚገጥማቸው የገንዘብ እጥረት የሚታደግ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ አግልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ “አራሼ” በተሰኘ የቁጠባ ሒሳብ ደብተር እንደ ደንበኛው ፍላጎት በወለድና ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚከፈት ልዩ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ነው፡፡
ባንኩ ከዚህ ቀደም ሴቶችን ማዕከል ያደረጉና ሴቶችን የሚያበረታቱ “ሉሲ”፣ “ፕሪሚየም ውሜን” እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ሥራ ለተሰማሩ ደግሞ “ታታሪ ሴት” የተሰኙ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶች እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በንብ “አራሼ” አዲስ የቁጠባ ሒሳብ ትውውቅ መርሃ ግብር ላይ የፌደራል እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች እና የባንካችን ተወካዮች ተሳታፊ ነበሩ፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!