በምክክር መድረኩ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር እመቤት መለሰን ጨምሮ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አስፈፃሚዎች፣ የዲስትሪክት ሀላፊዎች፣ የመምሪያ ዳይሬክተሮችና የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶክተር እመቤት ”ባንካችን አመታዊ አፈጻጸሙን እያካሔደ ያለበት ይህ ወቅት የቡሄ በዓል መሆኑን ተከትሎ ለመላው የባንካችን ማህበረሰብ የብርሃን አመት እንዲሆን እመኛለሁ” ብለዋል።
ባለፈው አመት የተለያዩ የአፈጻጸም ክፍተቶች የነበሩበት ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በቅርቡ ያከናወነውን ሪፎርም ተከትሎ ፈጣን ለውጥ ማስመዝገቡን ገልፀዋል።
አመታዊ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ቺፍ ኦፊሰር አቶ በላይ ጎርፉ ናቸው። በዚህም በአመቱ በነበሩ ክፍተቶች ላይ ፈጣንና ተገቢ እርምጃዎችን በመውሰድ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ለውጦች መምጣታቸውን ጠቁመዋል።
የበጀት አመቱንም ከብዙ ቁልፍ የአፈጻጸም ማሳያዎች አኳያ በተሻለ ብቃት ማጠናቀቅ መቻሉን አመላክተዋል። የምክክሩ ተሳታፊዎችም በባንኩ አጠቃላይ አፈጻጸም ላይ አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ።
በዚህም ከፍተኛ ለውጥ የመጣባቸው ዘርፎች ላይ አሁንም አጠናክሮ በመሥራት ባንኩን ወደ ቀደመ ከፍታውና ከዚያም ላቅ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!