በትላንትናው ዕለት በብሔራዊ ቤተ-መንግስት እውቅናና ሽልማት ከተበረከተላቸው 550 ታማኝ ግብር ከፋዮች መካከል ባንካችን አንዱ ሲሆን ለአራት ተከታታይ ዓመታት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ በመሆኑም ልዩ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
የባንካችን ቺፍ ፋይናንስና ፋሲሊቲስ ኦፊሰር አቶ ሳምሶን አምዲሳ የባንኩን እውቅናና ሽልማቱን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋል ፡፡
በመርሐ ግብሩ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተሸላሚዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መረጃውን ለሌሎች ስለሚያጋሩ እናመሰግናለን!
***
25 ዓመታት በታታሪነትና በአገልጋይነት!