ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ጋር በ2025/26 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክት አመራሮች ቤተሰቦች ጋር የምስጋና የእራት ምሽት ስነ ስርአት ትናንት ነሀሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት አካሄዷል።
ባንኩ የ2025/26 በጀት ዓመት “ጉዞ ወደ 2030 ለላቀ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መርሐ ግብር ላይ በበጀት አመቱ የላቀ አፈፃጸም ላስመዘገቡ 20 ቅርንጫፎችና 3 የዲስትሪክት አመራሮች ማበረታቻ ቃል ከተገቡ ጉዳዮች መካከል አንዱ ከባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ጋር የእራት ምሽት ዝግጅት ማካሄድ እንደነበረ ይታወሳል።
መርሐ ግብሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ የዛሬ ዕለት ልዩ ቀን መሆኑን ጠቅሰው የላቀ አፈፃፀም ላበረከቱ አካላት የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት የተጠበቀ መሆኑን በመጠቆም ልቆ መገኘት ሙሉ በሙሉ የቁርጠኝነትና የትጋት ውጤት ነው ብለዋል። አክለውም ስኬት በድንገት የሚመጣ አጋጣሚ ሳይሆን ከጀርባው በርካታ የማያቋርጡ ጥረቶችና በፈተና ውስጥ ያለመሸነፍ ፅናትና በተቋሙ ርዕይ መታመንን እንደሚጠይቅ ጠቅሰው፣ የላቀ ውጤት ላበረከቱ አካላት እውቅናና ምስጋና በማቅረብ መልካም የሥራ ዘመንና የእራት ምሽት ኘሮግራም ተመኝተዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ቅርንጫፎች፣ ዲስትሪክቶች እና ቤተሰቦቻቸው፣ የባንኩ ከፍተኛ የማኔጅመንት አመራረች የተገኙ ሲሆን ባሳለፉት ድንቅ የእራት ምሽትም ደስተኛ እንደነበሩ ገልጸዋል።



