ባንኩ በደሴ ከተማ ለሚኖሩና ገቢያቸው አነስተኛ ለሆነ የማኅበረሰብ ክፍሎች የትንሣኤ በዓል መዋያ ድጋፍ አድርጓል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የደ/ወሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ቆሞስ አባለይኩን ወንድይፍራው እንዲሁም በርካታ የሀይማኖት አባቶች እና የባንኩ አመራሮች በተገኙበት ድጋፍ ተደርጓል።
በመጨረሻም አባ ለይኩን ባንኩ ባደረገው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን በመጥቀስ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ባንኩ ባደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን በመጥቀስ ለተደረገላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ባንኩ የጀመረው የትንሳኤ በዓል ማኅበራዊ ኀላፊነት የመወጣት ተግባር በነገው እለትም በተለያዩ አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።




