N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀውና ከዛሬ መስከረም 19 እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በሚቆየው በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም 2026 ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

 

ፎረሙን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተው በይፋ አስጀምረውታል። በፎረሙ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዋች የተገኙ ሲሆን፣ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደም በመድረኩ ተገኝተዋል።

 

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በፎረሙ ላይ ተገኝቶ የንብተራ  ዲጂታል አገልግሎቶችን ማለትም ንበተራ ኦንላይን፣ ንብተራ ህንጻ አስተዳደር፣ ንብተራ አስኳላ፣ ንብተራ ሴቬንግ፣ ንብተራ ቨርቹል ካርድ እና ሌሎችንም ለተሳታፊዎችና ጎብኚዎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

 

በፎረሙ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የክፍያ አገልግሎት ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አማካሪ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎችም እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

 

***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs