ትናንት መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በተጀመረው በኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም-2026 ተገኝቶ ልዩ ልዩ አገልግሎቶቹን በማስተዋወቅ ላይ የሚገኘው ባንካችን ዛሬም ሁለተኛ ቀኑን በያዘው መርሃ ግብር ለደንበኞቹ አየሰጣቸው የሚገኙ የንብተራ ዲጂታል አገልግሎቶቹን፤ ለብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ጨምሮ ለፎረሙ ተሳታፊዎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። በፎረሙ የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደን ጨምሮ በርካታ ታዳሚዎች በዛሬው ዕለትም ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም -2026 እስከ ነገ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!



