N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው የ2025/26 የበጀት ዓመት ስኬታማ ውጤት አስመዘገበ፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በተጠናቀቀው የ2025/26 የበጀት ዓመት በዋና ዋና የሥራ አፈጻጸም መመዘኛዎች ስኬታማ ውጤት በማግኘት የተሳካ አፈጻጸም አስመዝግቧል።

 

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ የበጀት ዓመቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የተመዘገበው ውጤት ለባንኩ የስኬት ጉዞ አበረታች መነሻ መሆኑን ገልጸው ለዚህ ስኬት ከባንኩ ጎን የቆሙ ታማኝ ደንበኞችን፣ ክቡራን ባለአክሲዮኖችን፣ የቦርድ ዳይሬክተሮችን፣ የሥራ አመራሮችን፣ መላው የባንኩ ሠራተኞችን እና  ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡

 

ዋና ስራ አስፈጻሚው በቀጣይ የ2026/27 የበጀት ዓመት ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የተለመደው የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው የባንኩ አመራሮች እና ሠራተኞች አዲስ የተቀረፀውን የአምስት ዓመት ፍኖተ-ካርታ እና የሦስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ከዚህ በላቀ ጥረት በመተግበር ባንኩ የተነሳለትን ርዕይ ያሳኩ ዘንድ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs