Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው ለራቁ የጥበብ ባለሙያዎች ድጋፍ አደረገ፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ ገበታቸው ለራቁ የጥበብ ባለሙያዎች ድጋፍ አደረገ፡፡

የ2017 ዓ.ም አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ሩጂ ኢቨንትስ ከባንካችን ጋር ያዘጋጀው የዘመን መለወጫ(አበባየሽ ሆይ) የእቁጣጣሽ ዜማ ሥነ-ስርአት በባንካችን ፕሪምየም ቅርንጫፍ ተካሂዷል፡፡

በዚሁ መርሐ-ግብር የተገኙት የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት መለሰ ወደ ባንኩ ለመጡት የአርቲስቶች ስብስብ የ“እንኳን ደህና መጣችሁ” ንግግር አድርገዋል፡፡

በዚህም ሩጂ ኢቨንትስ በቅርቡ በምንቀበለው የአዲስ አመት ዋዜማ በተለያየ ችግር ከሙያ የራቁ የኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ባለውለታዎችን በማሰብ ላሰናዳው ዝግጅት አድናቆት በመቸር “ለዚህ የተቀደሰ ተግባር አጋርነት እኛን ስለመረጣችሁ፤ ወደኛ ስለመጣችሁ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም አመሰግናለሁ” ብለዋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተደጋጋሚ ጊዜያት ማህበራዊ ሀላፊነቶቹን በተለያዩ ዘርፎች በመወጣት ከሀገርና ህዝብ ጎን መሆኑን ያመላከተባቸው የድጋፍ መስኮች በርካታ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በጎ ተግባራትን በመደገፍ የጋራ ማህበራዊ ችግሮች እንዲቃለሉ ንብ ባንክ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ “ባንኩ ለጥበቡ ኢንደስትሪ ያለውን አድናቆትና ክብር ለመግለፅ” በሚል የ200,000(ሁለት መቶ ሺህ) ብር የገንዘብ ሥጦታ በማበርከት የ“መልካም አዲስ አመት” ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs