ባንኩ በመቐለ ከተማ ለሚኖሩና ገቢያቸው አነስተኛ ለሆነ የማኅበረሰብ ክፍሎች የትንሣኤ በዓል መዋያ ድጋፍ አድርጓል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት በትግራይ እርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃናት የደብረሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ገ/ህይወት እንዲሁም በርካታ የሀይማኖት አባቶች እና የባንኩ መቐለ ዲስትሪክት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ድጋፍ ተደርጓል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ባንኩ ላደረገላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ባንኩ የጀመረው የትንሳኤ በዓል ማኅበራዊ ኀላፊነት የመወጣት ተግባር ዛሬም በሌሎች አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።




