N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሆሳዕና ከተማ ሄጦ ቀበሌ ለሚገኙና ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች የትንሣኤ በዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ በሆሳዕና ከተማ ሄጦ ቀበሌ  ለሚኖሩ አቅመ ደካሞች፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከብር 4 መቶ  ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፍ አደረገ ።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የሆሳዕና ከተማ የሄጦ ቀበሌ አስተዳደር አቶ ታምራት ካሳ በሰጡት አስተያየት ለበርካታ አረጋዊያን ፣አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች ባንኩ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ስላበረከተው በጎ አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል። ባንኩ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ በዓላት ወቅት በቀበሌው ድጋፍ ለሚሹ አቅመ ደካሞች ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው ይህ የመረዳዳትና የመተጋገዝ ሰናይ ተግባር  ሁሌም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል ።

በመጨረሻም የሆሳዕና ዲስትርክት ዳይሬክተር አቶ ደርበው ሚካኤል በበኩላቸው ዲስትርክቱ በከተማና በሌሎች ዞኖችም ጭምር በተለያዩ በዓላት ወቅት ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ ያለው ባንክ እንደሆነ ገልጸዋል ።

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ባንኩ ላደረገላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs