N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ስፖንሰር ያደረገው የ“ኬሮድ” 6ኛው ዙር የ15 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ።

የኬሮድ 6ኛው ዙር 15 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ዛሬ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል። “ለሰላም አብረን እንሩጥ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ሰላምንና አንድነትን በስፖርት ለማጠናከር ያለመ ነው። በሩጫው ከ2 ሺህ በላይ አትሌቶች እና ከ45 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በውድድሩ የኢትዮጵያን ባንዲራ በተለያዩ የዓለም የስፖርት መድረኮች ያስተዋወቁ አትሌቶችም ተሳትፈዋል። የዝግጅቱ ዋና ስፖንሰር የሆነው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በመርሃ ግብሩ ላይ “ንብተራ” የዲጂታል ምርትና አገልግሎቱን ለተሳታፊዎች አስተዋውቋል። በዝግጅቱ የባንኩ ሪቴይልና ኤስኤምኢ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሙሉቀን ደምሴን ጨምሮ ሌሎች የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል። ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የኬሮድ ታላቁን ሩጫ ለተከታታይ አምስተኛ ዙር ስፖንሰር ማድረጉም ታውቋል።

 

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs