Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለ2 ቀናት ሲያከናውነው የነበረውን አመታዊ የማኔጅመንት የምክክር መድረክ አጠናቀቀ፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለ2 ቀናት ሲያከናውነው የነበረውን አመታዊ የማኔጅመንት የምክክር መድረክ አጠናቀቀ፡፡

 

በባንኩ የአራት ኪሎ ህንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲከናወን የቆየው የባንኩ አመታዊ የማኔጅመንት አፈጻጸም የምክክር መድረክ ሁሉም የባንኩ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች፣ የዲስትሪክት ሀላፊዎችና የዋና መሥሪያ ቤት የሥራ ሀላፊዎች የተሳተፉበት ነበር፡፡

 

በዚህም ባለፈው በጀት አመት ላጋጠሙ ክፍተቶች እርማት የተወሰደበት መንገድ የሚደነቅ ከመሆኑም ባሻገር ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማድረግ ባንኩን ይበልጥ ትርፋማ የሚያደርጉ አሰራሮችን መተግበር እንደሚገባ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት መለሰ አሳስበዋል፡፡

 

በተያዘው የበጀት አመት ባንኩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ዝግጅት እየተደረገባቸው በሚገኙ የዲጂታል እንዲሁም የመደበኛ የአገልግሎት ዘርፎች አዳዲስ መተግበሪያዎችና አሰራሮችን ይፋ ለማድረግ በመጨረሻ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎችም በውይይቱ የተገኙ ጠቃሚ ግብአቶችንና የሥራ አቅጣጫዎችን በመቀበል ባንኩን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
***

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

 

 

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs