N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ የተደረገው ዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው የ2019 ዓ.ም. የአዲስ ዓመት መርሐ ግብር ላይ ነው።

 

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤናና የስኬት ዓመት እንዲሆን ለደንበኞች፣ ባለአክሲዮኖች፣ ሠራተኞችና መላው ማኅበረሰብ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

 

ባንኩ ባለፈው ዓመት ላስመዘገበው ስኬት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ሄኖክ፣ በአዲሱ ዓመትም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሁሉን አቀፍ አገልግሎትን በማጠናከር የተሻለ ስኬት ለማስመዝገብ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

 

የማዕከሉ ተወካይና የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ዳዊት እሸቱ፣ ድጋፉ ሕፃናቱ አስፈላጊውን ሕክምና አግኝተው ወደ ተሻለ ሕይወት እንዲመለሱ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸው፣ ባንኩ በየዓመቱ ለሚያደርገው ድጋፍ ከልብ አመስግነዋል።

 

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs