ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ሀፃናት መርጃ ማዕከል የ250 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የልብ ህመም ችግር ያለባቸውን ህፃናት ህክምና እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ማዕከሉ በአሁን ሰዓት ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም ባንኩ ለማዕከሉ የገንዘብ ድጋፎችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ይህንኑ በጎ ተግባር በመቀጠል ዛሬ ጳጉሜ 05 ቀን 2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማን ምክንያት በማድረግ በማዕከሉ ህክምና ላይ ለሚገኙ ህፃናት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደም በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ይህ ድጋፍ ህፃናት በአዲስ ዓመት በአዲስ ተስፋ እና መልካም ምኞት እንዲጀምሩ ከመመኘት የመነጨ ነው ብለዋል።
የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ህሩይ ዓሊ በበኩላቸው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከማዕከሉ ጎን መሆን የሚያደርገውን በጎ ተግባር አመስግነው ድጋፉ ለልብ ታማሚ ህፃናት ተስፋ መሆኑን በመግለጽ አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንልን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
🌼 መልካም አዲስ ዓመት! 🌼
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!





