Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለአምስት ተከታታይ አመታት ታማኝ የግብር ከፋይ በመሆኑ የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማት ተበረከተለት፡፡

7ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ለታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ትናንት መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተካሄደበት ወቅት ባንካችን ታማኝ የግብር ከፋይ በመሆኑ በክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፕላቲኒየም ደረጃ የእዉቅና ሽልማት ተሰጥቶታል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ከመሥጠት በተጓዳኝ የሚጠበቅበትን ታማኝ ሀገራዊ የግብር ከፋይነት ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ እየተወጣ መሆኑ የተበረከተለት የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማት ማሳያ መሆኑን የጠቆሙት የባንኩ ዋና ሥራ  አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ በዚሁ አጋጣሚ ለመላው የባንካችን ባለአክሲዮኖች፣ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የማኔጅመንት አካላት፣ ሰራተኞችና ደንበኞች ሽልማቱ የጋራ ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባንካችን ለሰባት ተከታታይ አመታት የከፍተኛና የታማኝ ግብር ከፋይነት ሽልማቶች ሲበረከትለት የቆየ ሲሆን በቀጣይም የሚጠበቅበትን ተቋማዊ ሀላፊነት እየተወጣ ይቀጥላል፡፡

***
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

<p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs