ስምምነቱን በንብ ባንክ በኩል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሔኖክ ከበደ፤ በግሪን አግሮ ሶሉሽን በኩል ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ አቶ አብርሃም እንድርያስ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ሰኔ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ፈርመዋል፡፡
አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነቱ፣ የአገራችን ከፍተኛ ሕዝብ በተሰማራበት በግብርናው ዘርፍ ለሚደረገው ሥራ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የገለጹት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ፤ በቀጣይም የዘርፉን ተደራሽነት በማስፋት ባንኩ በአጋርነት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል፡፡
የግሪን አግሮ ሶሉሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አብርሃም እንድርያስ በበኩላቸው፣ ግብርናውን ለማዘመን የፋይናንስ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በመተባበርና በመተጋገዝ ውጤታማ ሥራ እንደሚሠራ እምነታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በሥነ ሥርአቱ ላይ የባንኩና የግሪን አግሮ ሶሉሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ መሆኑን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!






