ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ዛጎል ሲስተም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በቴክኖሎጂው ዘርፍ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ፈረሙ፡፡
በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው ሥነ ሥርአት ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚን በመወከል አቶ ግርማ ፈቀደ የሆልሴልና ሪቴይል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር፣ በዛጎል ሲስተም ትሬዲንግ በኩል የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ ንጉሤ በመግባቢያ ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡
ስምምነቱ፣ ከባንካችን ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረግ የአየር ትራንስፖርት የጉዞ ቲኬት በኦንላይን ለመቁረጥ የሚያስችል እንደሆነ በፊርማ ሥነ ሥርአቱ ላይ ተገልጿል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ቴክኖሎጂን መሠረት አድርገው ከሚሠሩ ተቋማት ጋር በትብብር በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አቶ ግርማ በሥነ ሥርአቱ ላይ ተናግረዋል፡፡




