Internet Banking
Internet Banking

”ንብ ባንክ ክፍተቶቹ ላይ ፈጣን እርማት በማድረግ ወደሚገባው ላቅ ያለ ደረጃ እየገሰገሰ ያለ ባንክ ነው”-የቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ ሺሰማ።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የባለአክስዮኖች 25ኛ መደበኛና 21ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።

 

በጉባኤው የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ የበጀት አመቱን የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

 

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች ለመፍታትና ወደነበረበት ደረጃ ለመመለስ እንደ አዲስ የተሰየመው የሥራ አመራር ቦርድና የሥራ አስፈጻሚ አካላት የተለያዩ የማሻሻያ እቅዶችን ተፈፃሚ በማድረግ ዋና ዋና ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

 

በተከታታይ በተደረጉ የሃብት ማሰባሰብ ጥረቶች ባንኩ የነበረበትን የጥሬ ገንዘብ እጥረት በመፍታት የጥሬ ገንዘብ ክምችትን ወደማሻሻል ደርሷል ያሉት ሊቀመንበሩ፤ በጀት አመቱ ደንበኞች በRTGS ወደ ሌሎች ባንኮች ከሚያደርጉት የገንዘብ ዝውውር ጋር ተያይዞ የነበረውን ጫና ማስተካከል መቻሉንም ገልፀዋል።

 

በዚህም ሳይከፈሉ የቆዩ ክፍያዎችን በመፈፀም የደንበኞችን አመኔታ መመለስ ተችሏል ብለዋል።

 

ውጤታማ የወጪ ቅነሳ ሥልቶችን ተፈፃሚ በማድረግ ከፍተኛ የሃብት ብክነትን ማስቀረት መቻሉን በመጥቀስ የሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቶችን በማሻሻል ደንበኞች ሂሳባቸውን በቀላሉ ማንቀሳቀስ መቻላቸውን ሊቀመንበሩ ገልፀዋል።

 

በነዚህና ሌሎች ፈጣን የእርማት እርምጃዎች ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በጀት አመቱን በትርፍ በማጠናቀቅ ወደሚገባው ላቅ ያለ ደረጃ እየገሰገሰ መሆኑን አመላክተዋል።

በቀጣይም በ2024/25 በጀት አመት ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ አዲስ የስትራቴጂ እቅድ በማውጣት የባንኩን እድገትና ተወዳዳሪነት ለማስቀጠል ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።

 

 

<p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs