ባንካችን ድሬዳዋ ከተማ ከሚገኙ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ያካሄደ ሲሆን በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የደንበኞቹን ፍላጎት ከምንጊዜውም በላይ ይበልጥ ለማሳደግና አገልግሎቱን ይበልጥ ተራሽ ለማድረግ የሦስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ነድፎ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በሌላም በኩል በምክክር መድረኩ በባንኩና በደንበኞች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና የደንበኞቹን ፍላጎቶች በተገቢው መንገድ ለማሟላት እንዲረዳ ባንካችን በአገልግሎት ጥራት ላይ በከፍተኛ ደረጃ እየሠራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቱን ይበልጥ በማዘመን የንብተራ ኦንላይ መተግበሪያን ጨምሮ የንብ ኢ-ብር፣ የንብተራ ፖስ እንዲሁም ንብተራ ኪውአር የክፍያ መንገዶችን ይበልጥ በማዘመን ለደንበኞች መቅረቡን በምክክር መድረኩ ላይ ተመላክቷል፡፡
በዚሁ የምክክር መድረኩ ላይ የተገኙ ደንበኞችም የተለያዩ አስተያየቶችና ሐሳቦችን ያነሱ ሲሆን የባንኩ ከፍተኛ የማኔጅመንት አካላት ከደንበኞቹ ጋር በዚህ ልክ በመቀራረብ ለመመካከርና ግንዛቤ ለመስጠት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!








