Internet Banking
Internet Banking

ባንካችን “በንብተራ እንሸላለም” መርሃ ግብር ላለፉት ሦስት ሳምንታት ለተሳተፉ  ደንበኞች የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት አካሄደ፡፡

የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ዛሬ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና  መ/ቤት በተካሄደበት ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉትና እድለኞችን እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ያበሠሩት የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ በላይ ጎርፉ፤ ባንካችን ፈጣንና አስተማማኝ የሆነውን “ንብተራ ኦንላይን” መተግበሪያን አበልጽጎ ወደ ሥራ ሲያስገባ፣ በታሳቢነት ካስቀመጣቸው ዓላማዎች ዋነኛው ሁሉም የባንኩ ደንበኞች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያሰፈልጋቸውን ዋና ዋና የባንክ አገልግሎት ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው፤ በመረጡት ሰዓት እና ባሉበት ሥፍራ ሆነው ግብይቶችን እና ክፍያዎችን እንዲሁም የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን በቀላሉ በእጅ ስልካቸው ለመፈፀም እንዲያስችላቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

የ“ንብተራ እንሸላለም” መርሃ-ግብርም፣ ደንበኞች መተግበሪያውን እንዲጠቀሙ በሽልማት ማበረታታት መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን ለሶስት ሳምንታት ሲካሄድ የነበረው የመጀመሪያ ዙር ሳምንታዊ የእጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታብሌትና የሞባይል ስልኮች ለደረሳቸው ዕድለኞች “እንኳን ደስ ያላችሁ!” በማለት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። እጣው በየሳምንቱ የሚወጣና ቀጣይነት ያለው በመሆኑ ደንበኞች መተግበሪያውን ሲጠቀሙ ባለዕድል የሚሆኑባቸውን የእድል ቁጥሮች የሚያገኙ ሲሆን በሌላም በኩል በንብተራ ኦንላይን መተግበሪያ ውስጥ የ’ንብተራ ሰፒንን’ በመጫወት ብቻ የበርካታ ሽልማቶች ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ አመልክተዋል፡፡

 

በዛሬው የመጀመሪያው ዙር የዕጣ አወጣጥ መርሃ-ግብር የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች እና የብሔራዊ ሎተሪ ተወካዮች ተገኝተዋል። በቀጣይም ዕድለኞች የደረሳቸውን ታብሌቶችና የሞባይል ስልኮች የሚረከቡ ይሆናል፡፡

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs