ባንካችን በባህር ዳር ከተማ ለሚኖሩና ገቢያቸው አነስተኛ ለሆነ የማኅበረሰብ ክፍሎች የትንሣኤ በዓል መዋያ ድጋፍ አድርጓል።
የድጋፍ መርሐ ግብሩ በባህርዳር ከተማ በተከናወነበት ወቅት የከተማው ቤተከህነት ኃላፊ ሊቀ ህሩያል ለይኩን አበበ ተገኝተው አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሀይማኖት አባቶች እና የባንካችን ባህርዳር ዲስትሪክት ኃላፊ ለተመረጡና ድጋፍ ለሚፈልጉ የህብረተሠብ ክፍሎች ለበዓል መዋያ የሚያገለግሉ የተለያዩ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች አበርክተዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ባንኩ ላደረገላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ባንኩ የጀመረው የትንሳኤ በዓል ማኅበራዊ ኀላፊነት የመወጣት ተግባር በተለያዩ አካባቢዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።



