ውድ ደንበኛችን፤
ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በተጻፈ ደብዳቤ ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሚፈጸሙ ግብይቶች በደንብ ቁጥር 576/2018 ላይ በተጠቀሰው የማስከፈያ ስሌት መሰረት ከደንበኞች ላይ ክፍያዎችን በመሰብሰብ በብሔራዊ ባንከ በተያዘው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ፅ/ቤት ሂሳብ ገቢ እንዲያደርጉ ለሁሉም ባንኮች ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባንካችን ከሚሰጠው ማንኛውም አይነት መደበኛ ብድር ላይ የሚሰጠውን የብድር መጠን 1% (አንድ በመቶ)፣ እንዲሁም በሁሉም የባንካችን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ከሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ላይ 5% (አምስት በመቶ) እየተጨመረ የሚሰበስብ መሆኑን በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ለበለጠ መረጃ አቅራቢያዎ የሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ወይም የባንኩን ጥሪ ማእከል 9698 በነጻ በመደወል ያናግሩ፡፡
***
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!





