N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

መረጃ ላልሰጣችሁ የባንካችን ባለአክሲዮኖች በሙሉ፤

ባንካችን በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 እና መመሪያ ቁጥር 1047/2017 መሠረት፣ አክሲዮኖችን ወደ ማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግምጃ ቤት አስተላልፎ በኤሌክትሮኒክስ ይዘት ለመተካት አስፈላጊውን መረጃ በመሰብሰብ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም እስካሁን መረጃ ያልሰጣችሁ፡-

  • የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ያወጣችሁ ባለአክሲዮኖች መታወቂያውን ወይም ፋይዳ ለማውጣት ምዝገባ ስታከናውኑ በአጭር የፅሑፍ መልዕክት የተላላከላችሁን ባለ 16 አኃዝ ቁጥር በመያዝ፤
  • እንዲሁም ነዋሪነታችሁ በውጭ ሀገር ሆኖ እስካሁን የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ያላወጣችሁ ባለአክሲዮኖች በፓስፖርታችሁ መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን አውቃችሁ፤

በተወካያችሁ አማካኝነት ወይም በአካል በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ፣ ወይንም በዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባለአክሲዮኖች አስተዳደር ዋና ክፍል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን ቅጽ እንድትሞሉ እየጠየቅን፤ ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ቅጹን ለመሙላት የምትችሉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የምትኖሩ ባለአክሲዮኖች ከታች በተገለፁት ስልክ ቁጥሮች ወይም የኢሜይል አድራሻዎች ብታሳውቁን ቅጹን የምንልክላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ቅጹን ካልሞላችሁ መረጃችሁ ወደ ማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግምጃ ቤት የማይተላለፍ በመሆኑ፣ በቀጣይ ከአክሲዮን ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን ለማግኘት የምትቸገሩ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

አድራሻዎች፡

  • ስልክ ቁጥሮች፡ 0115-549015 0115-578974 ወይም 0911-765646
  • Email Gedion.Debebe@nibbank.com.et / Alem.Taye@nibbank.com.et
Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs